ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (Mesgana Siyanseh New) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው (፪x)

ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x)

እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው
ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

ሠማያዊ ፡ ብርሃን ፡ በልቤ ፡ ውስጤ ፡ በርቷል
የጌታዬ ፡ ማዳን ፡ ነፍሴን ፡ አግኝቷታል
ከዘለዓለም ፡ ጥፋት ፡ ከፍርድ ፡ አምልጫለሁ
በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ አዲስ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ

ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ
ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x)

ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው

ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x)

እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው
ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

ክቡር ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ የእስራኤል ፡ ተዋጊ
በአለቀ ፡ ሰዓት ፡ ላይ ፡ የምስደርስ ፡ ታዳጊ
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ በሥልጣንህ ፡ ሽረህ
በድል ፡ አራመድከኝ ፡ ታሪኬን ፡ ቀይረህ

ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ
ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x)

ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው

ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x)

እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው
ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

ፊትህ ፡ እቀርባለሁ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና
ጌታ ፡ ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ የለኝምና
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ እንካ ፡ ተቀበለው
ሕያው ፡ መስዕዋቴ ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው

ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ
ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x)