ለእኔ ፡ የምታስበው (Lenie Yemetasebew) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

አሻግሬ ፡ አያለሁ ፡ ያንተን ፡ መልካምነት
ከቶ ፡ አልገምትህም ፡ አሁን ፡ ባለሁበት
ታሪክ ፡ የምትለውጥ ፡ ሁሉንም ፡ የምትቀይር
እኔ ፡ የማመልክህ ፡ ድንቅነህ ፡ እግዚአብሔር

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)

የተገለጠውን ፡ ነገር ፡ ጸራለህ
በላይ ፡ ተሰውረህ ፡ ድንቅን ፡ ታደርጋለህ
ተዐምራትህ ፡ ብዙ ፡ እጅግ ፡ የበዛ ፡ ነው
ጌታ ፡ አሰራርህ ፡ ከሁሉም ፡ ልዩ ፡ ነው

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)

ከሁኔታዎች ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ አምናለሁ
ሚሰማኝን ፡ ሳይሆን ፡ የሩቁን ፡ አያለሁ
ከእንግዲህ ፡ ታምኜ ፡ በእምነት ፡ እኖራለሁ
የተናገርከኝንም ፡ እንዳገኝ ፡ አውቃለሁ (፪x)

ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሳለ ፡ ጠላቶች ፡ ቢዋሹም
አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ከቶ ፡ አትለወጥም
መልካምነትን ፡ በማድረግ ፡ ደስ ፡ ይለሃልና
አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)
አመሰግንሃለሁ (፫x)