Endalkachew Hawaz/Mesganawen Alresawem/Kef Bel
ከጥንት እንደሰማሁት
በዓይኖቼም ደግሞ እንዳየሁት
አምላክ ከአንተ በቀር የለም
መቼም ቢሆን አይገኝም
በምድር ሆነ በሠማይ
በየብስ ሆነ በባሕር ላይ
በሰው ልጆችም መካከል
የለም አንተን የሚስተካከል
አዝ
ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፬x)
አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም
ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (፪x)
ሰዎች የሚያመልኳቸው
ዛሬም የሚከተሏቸው
ብዙ አማልክት ቢኖሩም
አንዳቸውም እውነት አይደሉም
ታላቅ ገናና ኃይለኛ (ገናና ኃይለኛ)
ታጋሽ መሃሪ የሆንህ
ከጥንት ከጥንትም ጀምሮ (ጀምሮ)
በእውነት እግዚአብሔር አምላክ ነህ
አዝ
ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፬x)
አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም
ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም
ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (፪x)
በእኔ ላይ ተሹመሃል
ፍቅርህ ልቤን ወርሶታል
እውነት በርታልኛለች
ነፍሴም አምላኳን አውቃለች
ውዴ አንተ የእኔ ነህ
እኔም የአንተ ሆኛለሁ
በቀረልኝ ዘመን ሁሉ
ሳደንቅህ ሳከብርህ ኖራለሁ
አዝ
ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፰x)