ሃሌሉያ (Hallelujah) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

በመጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ውስጥ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አለ ።
እግዚአብሔር ፡ አምልኮንና ፡ ምሥጋናን ፡ ይወዳል ።
ግዑዛን ፡ ፍጥረታት ፡ እንኳን ፡ ይህን ፡ ተረድተው ፡
ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ሳያቋርጡ ፡ ያመልኩታል ።
የእጆቹ ፡ ሥራ ፡ የሆንንና ፡ ፍቅሩን ፡ ያየን ፡ እኛማ ፡
እንዴት...

ቀን ፡ ለቀን ፡ ነገርን ፡ ታወጣለች
ሌሊት ፡ ለሌሊቱ ፡ ቀትር ፡ ትናገራለች
ድምጻቸውን ፡ ከቶ ፡ ሳያሰሙ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ሲያዜሙ
እኔም ፡ ልቤ ፡ በዚህ ፡ ተደነቀ
የምሥጋና ፡ ዜማ ፡ አፈለቀ

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
(ሃሌሉያ) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
(ክብር ፡ ለአንተ ፡ ኢየሱስ) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
(ሃሌሉያ)

ዓይኖቼን ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አቀናለሁ
እጆቼን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

ሠማያት ፡ ክብርህን ፡ ያሳየሉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ እያሉ ፡ ይናገራሉ
ሰነፍ ፡ በልቡ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ቢልም
የዓለም ፡ ምስክር ፡ እራስህን ፡ አልተውክም
የማይታየው ፡ ባሕሪህ ፡ ታይቷል
ለዘለዓለም ፡ ኃይልህም ፡ ተገልጧል

ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉያ

ፀሐይም ፡ . (1) . ፡ ታወጣለች
እስከ ፡ ምድር ፡ ዳርቻም ፡ ድረስ ፡ ታዞራታለህ
ከዋክብርትም ፡ በሌ'ት ፡ የምትመራ
የጨረቃን ፡ ብርሃን ፡ የምታበራ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ማነው
በህዋ ፡ ላይ ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ

ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉያ
ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ)
ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፫x)

ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ በሠማይና ፡ በምድር ፡
መካከል ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ ።
እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም ።
በሠማይም ፡ የለም ፤ በምድርም ፡ የለም ።
ታላቅነት ፡ ገናናነት ፣ ክብር ፣ ምሥጋና ፣
ባለጠግነት ፡ ሁሉ ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ።
አሜን !

ዓይኖቼን ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አቀናለሁ
እጆቼን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)