አሜን ፡ ይገባሃል (Amien Yegebahal) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

የምሥጋናን ፡ መስዋዕት ፡ እሰዋለሁ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ አቀርባለሁ
እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ አምላክ ፡ ነህና
ልትወደስ ፡ ይገባሃልና (፪x)

ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x)

. (1) . ፡ በበገና
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በምሥጋና
እቀኝልሃለሁኝ ፡ በክብሬ
ዝማሬም ፡ ይፈልቃል ፡ ከከንፈሬ

ክብር ፡ ለአንተ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ላንተ (፬x)
ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x)

ያደረጋትን ፡ ድንቅ ፡ ልጸሙ
በአደባባዮቹ ፡ የምትቆሙ
እስኪ ፡ ተቀኙለት ፡ ለዚህ ፡ ጌታ
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ በደስታ

ክብር ፡ ለአንተ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ላንተ (፬x)
ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x)

ሠማያትን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
የምድርን ፡ መሰረት ፡ ያጸናህ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
ባሕሩንና ፡ የብሱን ፡ የለየህ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
የብርታትህን ፡ ጉልበት ፡ ያሳየኸን
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)

ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x)

ዙፋንህ ፡ ከጥንት ፡ ከዘለላለም
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የሚመስለህ ፡ የለም
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
የሁሉ ፡ አዛዥ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)
እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን)

ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x)