አመሰግንሃለሁ (Amesegenehalehu) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

አዝአመሰግንሃለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ አመሰግንሃለሁ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ታከብርሃለች ፡ ሁልጊዜም ፡ ትባርክሃለች
መልካም ፡ ነህና ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ በዘመኔ
መልካም ፡ ነህና ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ በዘመኔ

እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት ፡ እንዳሳቡም ፡ ለተጠሩት
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ የሚደረገው ፡ የሚሆነው
እኔም ፡ አየሁ ፡ መልካምነትህን
ለሚታገሱ ፡ ቸር ፡ መሆንህን (፬x)

አዝአመሰግንሃለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ አመሰግንሃለሁ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ታከብርሃለች ፡ ሁልጊዜም ፡ ትባርክሃለች
መልካም ፡ ነህና ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ በዘመኔ
መልካም ፡ ነህና ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ በዘመኔ

በጐነትህን ፡ ለመናገር ፡ ቸር ፡ መሆንህንም ፡ ለመመስከር
አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ እላለሁ
በምሥጋና ፡ ልዘምርልህ ፡ አዲስን ፡ ቅኔም ፡ ልቀኝልህ (፪x)