አቤቱ ፡ ውበትህን (Abietu Webetehen) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ታላቅነትህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ የሚያበራ
ድምጽህ ፡ ነጐድጓድ ፡ ነው ፡ የሚያስፈራ
ደረትህን ፡ በወርቅ ፡ የታጠቀ
እጅግ ፡ ያማረ ፡ ነው ፡ ውበትህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ እያደነቀ
አቤቱ ፡ ሥራህን ፡ እያደነቀ
ታላቅነትህን ፡ እያደነቀ
ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ ይኸው ፡ አፈለቀ (፪x)

እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ
መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ
አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ

የቤትህን ፡ ስርዓት ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ፡ ጥበብህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
የቤትህን ፡ ስርዓት ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ፡ ጥበብህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)

ስለ ፡ አንተ ፡ ከሰማሁት ፡ ዝና ፡ ይልቅ
በዓይኔ ፡ የማየው ፡ ሆነብኝ ፡ ድንቅ
ስለዚህም ፡ ነፍሴ ፡ ተማረከች
የምሥጋናን ፡ ዜማ ፡ አፈለቀች

አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ (አቤቱ ፡ ውበትህ) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ)
አቤቱ ፡ ሥራህን ፡ (አቤቱ ፡ ሥራህን) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ)
ታላቅነትህን ፡ (ታላቅነትህን) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ)
ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ (ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን)
ይኸው ፡ አፈለቀ ፡ (ይኸው ፡ አፈለቀ) (፪x)

እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ
መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ
አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ

የእጆችህን ፡ ሥራ ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ፡ ፍጥረታትን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x)
ጨረቃና ፡ ፀሐይ ፡ ከዋክብት
በምድር ፡ ላይ ፡ ያሉ ፡ እንስሳት
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ለአንተ ፡ ተፈጥረዋል
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ያስደንቃል

አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ እያደነቀ
(አቤቱ ፡ ሥራህ) ፡ አቤቱ ፡ ሥራህ ፡ እያደነቀ
(ታላቅነትህን) ፡ ታላቅነትህን ፡ እያደነቀ
ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ ይኸው ፡ አፈለቀ (፪x)

እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ
መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ
አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ