መታደል ፡ ነው (Metadel New) - እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 5.jpg


(5)

ክብርህን ፡ አሳየኝ
(Kebrehen Asayegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ከአንተ ፡ እንደመኖር ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ነለም
አንተን ፡ እንደማክበር ፡ ያለ ፡ ክብር ፡ የለም
ከአንተ ፡ እንደመኖር ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ነለም
አንተን ፡ እንደማክበር ፡ ያለ ፡ ክብር ፡ የለም ፡ የለም

ፈቃድህን ፡ እንደማድረግ ፡ ያለ ፡ ስኬት ፡ የለም
በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ እንደማደግ ፡ ያለ ፡ ደስታ ፡ የለም

ኑሮዬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ክብሬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ስኬቴም ፡ ይሄ ፡ ነው
ደስታዬም ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)

በጐና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኘውን
ፈቃድህን ፡ ፍፁም ፡ የሆነውን
አድርጐ ፡ ለዚያ ፡ ኖሮ ፡ ማለፍ
መታደል ፡ ነው ፡ በጥላህ ፡ ስር ፡ ማረፍ
እንዴት ፡ ያለ ፡ መታደል ፡ ነው ፡ መታደል ፡ ነው ፡ መታደል ፡ ነው (፬x)

ኑሮዬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ክብሬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ስኬቴም ፡ ይሄ ፡ ነው
ደስታዬም ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)

በአንተ ፡ ዘንድ ፡ እጅግ ፡ የከበረ
ነውና ፡ ፍጻሜው ፡ ያማረ
በሰማይ ፡ አለው ፡ ታልቅ ፡ ዋጋ
ለአንተ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ በአንተው ፡ ፀጋ
እንዴት ፡ ያለ ፡ መታደል ፡ ነው ፡ መታደል ፡ ነው ፡ መታደል ፡ ነው (፬x)

ኑሮዬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ክብሬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ስኬቴም ፡ ይሄ ፡ ነው
ደስታዬም ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)

ደስታዬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ስኬቴም ፡ ይሄ ፡ ነው
ክብሬም ፡ ይሄ ፡ ነው
ኑሮዬም ፡ ይሄ ፡ ነው