ምን ፡ አደርግ ፡ ዘንድ ፡ ትወዳለህ (Men Aderg Zend Tewedaleh) - እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 5.jpg


(5)

ክብርህን ፡ አሳየኝ
(Kebrehen Asayegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ክብሩን ፡ ጥሎ ፡ እስከመስቀል ፡ ሞት ፡ እንደታዘዘህ ፡ እንደኢየሱስ
ረብ ፡ ያልነውን ፡ ትምክህቱን ፡ እንደተወልህ ፡ እንደፓውሎስ
በገዛ ፡ ዘመኑ ፡ ታዞ ፡ ሃሳብህን ፡ እንዳገለገለህ ፡ እንደዳዊት

አዝ፦ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ
ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ
አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ
ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ
ምን ፡ አደርግ ፡ ዘንድ ፡ ትወዳለህ (፬x) ፡ ትወዳለህ

በግብጽ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ይልቅ ፡ ሙሴ ፡ መከራውን ፡ መረጠ
ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ ተመልክቶ ፡ ያንን ፡ አስመለጠ
ለሃሳብህ ፡ ታዞ ፡ መንገድህን ፡ ይዞ ፡ እስከመጨረሻው ፡ ተከትሎህ ፡ ሮጠ

አዝ፦ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ
ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ
አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ
ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ
ምን ፡ አደርግ ፡ ዘንድ ፡ ትወዳለህ (፮x) ፡ ትወዳለህ