ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ይሁን (Kebreh Benie Lay Yehun) - እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 5.jpg


(5)

ክብርህን ፡ አሳየኝ
(Kebrehen Asayegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ውኃን ፡ የተጠማ ፡ ሰው
ሳይጠጣ ፡ እንደማይረካ
እኔም ፡ ተጠምቼሃለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)

ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ይሁን (፪x)
ኦ ፡ ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ይሁን (፪x)

ሌላውማ ፡ አያጠግበኝ ፡ እኔን
ሌላውማ ፡ አያረካው ፡ ልቤን (፪x)

ሁሉን ፡ አየሁ ፡ ግን ፡ እንደአንተ ፡ የከበረ
አላገኘሁ ፡ አላገኘሁ (፪x)
ምን ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ከአንተ ፡ የሚወዳደር
ልኖርለት ፡ የሚገባኝ ፡ ከክብርህ ፡ በስተቀር

ሌላውማ ፡ አያጠግበኝ ፡ እኔን
ሌላውማ ፡ አያረካው ፡ ልቤን (፪x)

የባሕሪው ፡ ምሳሌ ፡ የክብሩ ፡ ነጸብራቅ ፡ የሆንከው
ከአባትህ ፡ እቅፍ ፡ የወጣሀው
ኢየሱስ ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው (፫x)
የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው