አንተን ፡ ብቻ ፡ ባገኝ (Anten Becha Bagegn) - እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 5.jpg


(5)

ክብርህን ፡ አሳየኝ
(Kebrehen Asayegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ ደስታዬ ፡ ነህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ እረፍቴ ፡ ነህ
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ምን ፡ ምን ፡ ሕይወት ፡ አለ
ከአንተ ፡ ውዲያስ ፡ ምን ፡ ምንስ ፡ ክብር ፡ አለ (፪x)

ሁሉን ፡ አግኝቼ ፡ አንተን ፡ ከማጣ
ሁሉን ፡ ነገር ፡ ኖሮኝ ፡ ክብርህ ፡ ከሚጐድልብኝ (፪x)
ሁሉን ፡ አጥቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ባገኝ
ይሄ ፡ ትርፌ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይህ ፡ ነው
ሁሉን ፡ አጥቼ ፡ ኢየሱስን ፡ ባገኝ
ይሄ ፡ ትርፌ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይህ ፡ ነው

ረቢ ፡ ያልኩትን ፡ ወዲያ ፡ እየጣልኩኝ
በፍፁም ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ እየፈለኩኝ
የሚታየውን ፡ የዓለምን ፡ ነገር
ትቼ ፡ እሮጣለሁ ፡ ላገኝ ፡ የአንተን ፡ ክብር (፪x)

ሁሉን ፡ አግኝቼ ፡ አንተን ፡ ከማጣ
ሁሉን ፡ ነገር ፡ ኖሮኝ ፡ ክብርህ ፡ ከሚጐድልብኝ (፪x)
ሁሉን ፡ አጥቼ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ባገኝ
ይሄ ፡ ትርፌ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይህ ፡ ነው
ሁሉን ፡ አጥቼ ፡ ኢየሱስን ፡ ባገኝ
ይሄ ፡ ትርፌ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይህ ፡ ነው

ህልውናህ ፡ መገኘትህ ፡ ሃልዎትህ
ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይህ ፡ ነው (፪x)