ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ና (Wede Eyesus Na) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 3.jpg

(3)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
(Egziabhier Teleq New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ሰው ፡ ዓለምን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል (፪x)
ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡ ነው (፪x)
ሰው ፡ ዓለምን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል (፪x)
ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡ ነው (፪x)

ከኢየሱስ ፡ ውጪ ፡ ኑሮ ፡ ኑሮ ፡ መች ፡ ያረካል
ሰው ፡ አምላኩን ፡ ሳያውቅ ፡ እንዴት ፡ እረፍትን ፡ ያገኛል (፪x)
እኔ ፡ ግን ፡ መስቀሉን ፡ ተሸክሜያለሁ (፪x)
አካሄዴን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ይሄው ፡ አድርጌያለሁ (፪x)

ና ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ና
ሕይወት ፡ ይሻልሃልና (፪x)
እናንተ ፡ ደካሞች ፡ ሸክም ፡ የከበዳችሁ
ኑ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይላል ፡ ጌታ ፡ ሊያሳርፋችሁ (፪x)

ሰው ፡ ዓለምን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል (፪x)
ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡ ነው (፪x)
ከኢየሱስ ፡ ውጪ ፡ ኑሮ ፡ ኑሮ ፡ መች ፡ ያረካል
ሰው ፡ አምላኩን ፡ ሳያውቅ ፡ እንዴት ፡ እረፍትን ፡ ያገኛል (፪x)

እኔ ፡ ግን ፡ መስቀሉን ፡ ተሸክሜያለሁ (፪x)
አካሄዴን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ይሄው ፡ አድርጌያለሁ (፪x)
ሞት ፡ ወይም ፡ ሕይወት ፡ ነው ፡ ከፊትሽ ፡ ያለው
ምንድነው ፡ ምትመርጪው (፪x)

በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ ጌታ ፡ አንቺን ፡ ይወድሻል
ምርጫሽን ፡ አስተካክይ ፡ እህቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል
በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ ጌታ ፡ አንቺን ፡ ይወድሻል
አሁኑኑ ፡ ወስኚ ፡ እህቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል