ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ (Kehulu Belay Neh Gieta) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 3.jpg


(3)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
(Egziabhier Teleq New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

 
ሰላምህ ፡ በዝቶልኛል ፡ አንተን ፡ ከአገኘሁ ፡ ጀምሮ
ሕይወቴ ፡ ተለውጧል ፡ ተቀይሯል ፡ የእኔስ ፡ ኑሮ
አንተን ፡ በመከተሌ ፡ ከአንተም ፡ ጋር ፡ በመሆኔ
ተጸጽቼ ፡ አላውቅም ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፭x)

አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ
ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ
መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)

የጐደለብኝ ፡ የለም ፡ ሁሉ ፡ ሞላልኝ ፡ እንጂ
በረከት ፡ እንደሁ ፡ አያልቅም ፡ ከአንተ ፡ ቤት ፡ ከአንተ ፡ ደጅ
የሰላም ፡ አለቃ ፡ ሆይ ፡ የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ ነህ
ማንም ፡ አይመጥንህም ፡ ከምርጦች ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፭x)

አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ
ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ
መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ (በላይ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
ከሁሉ ፡ በላይ (ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (ጌታ) (፪x)

ከምን ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማን ፡ ጋር ፡ ላስተካክልህ
ከሚታይ ፡ ከማይታየው ፡ ከሁሉ ፡ ትበልጣለህ
ከሁሉ ፡ ትበልጣለህ (አው ፡ ከሁሉ) ፡ ከሁሉ ፡ ትሻላለህ (ሁሁ)
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ (እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ) ፡ ለዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ (፭x)

አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ
ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ
መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ (ኦ ፡ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ
ከሁሉ ፡ በላይ (ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ)
ከሁሉ ፡ በላይ (ቃልህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
(ክብርህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ መንግሥትህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ)
ከሁሉ ፡ በላይ (ሥጋህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ
ከሁሉ ፡ በላይ (ፍቅርህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ)
ከሁሉ ፡ በላይ (ኦ ፡ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ከሁሉ ፡ በላይ (በላይ ፡ በላይ) (፪x)