From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
ለክብሩ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
ለኃይሉ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው (፪x)
እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ
የክብሩን ፡ ብዛት ፡ ግርማውን ፡ እያየሁ
እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ
የኃይሉን ፡ ችሎት ፡ ብርታቱን ፡ እያየሁ (፪x)
በጠባባ ፡ አይምሮዬ ፡ አልችልም ፡ ልገምተው
እስካሁን ፡ ካወቅሁት ፡ በላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነው
እንኳን ፡ ማንነቱ ፡ ቀርቶ ፡ ስራውም ፡ አይመረመር
ከተባለው ፡ ሁሉ ፡ ያልፋል ፡ ይበልጣል ፡ የአምላኬ ፡ ክብር
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልናገር
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልመስክር
ቃላት ፡ ባጣም ፡ እንዲያው ፡ ላመስግነው
አምልኮዬ ፡ እርሱን ፡ ባይመጥነው (፪x)
ግርማው ፡ እጅግ ፡ የሚያስፈራ ፡ ታላቅ ፡ ስሙ ፡ የገነነ
ደግሞ ፡ መሃሪ ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ የፍቅር ፡ ጌታ ፡ የሆነ
ብርሃንን ፡ ተጐናጽፎ ፡ ማደሪያውን ፡ በክብር ፡ የሞላ
እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ አምላክስ ፡ የታለ ፡ ሌላ
ትልቅ/ታላቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ/ታላቅ ፡ ነው
ለክብሩ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው
ታልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ታልቅ ፡ ነው
ለኃይሉ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው (፪x)
እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ
የክብሩን ፡ ብዛት ፡ ግርማውን ፡ እያየሁ
እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ
የኃይሉን ፡ ችሎት ፡ ብርታቱን ፡ እያየሁ (፫x)
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልናገር
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልመስክር
ቃላት ፡ ባጣም ፡ እንዲያው ፡ ላመስግነው
አምልኮዬ ፡ እርሱን ፡ ባይመጥነው (፪x)
|