የአንተን ፡ ኪዳን (Yanten Kidan) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ
ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ
አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ (፪x)

በኢየሱስ ፡ ታመኑ ፡ ዛሬም ፡ እላለሁ
ዘንዶው ፡ ሲያዋርድ ፡ ሲጥል ፡ ስላየሁኝ
ላዘነው ፡ መጽናኛ ፡ ላለቀሰው ፡ ደስታ
አስታዋሽ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ቀድሞም ፡ ለተረሳ
(፪x)

አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ
ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ
አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ

ኢየሱስ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ከምንም ፡ በላይ
ለነፍሴ ፡ መጽናኛ ፡ ሆኗል ፡ ኤልሻዳይ
አታዋኪ ፡ ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ለአንቺ ፡ የሰራልሽ ፡ የለውም ፡ ተተኪ
(፪x)

አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ
ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ
አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ

የጨለማው ፡ ወራት ፡ አለፈ ፡ እንደዋቃ
ቃል ፡ ይዤ ፡ ስወጣ ፡ በነነ ፡ እንደ ፡ ጤዛ
ነፍሴም ፡ አስታወሰኝ ፡ ያደረገላትን
ወደ ፡ እርሱ ፡ ቀረበ ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮን
(፪x)

አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ
ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ
አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ