ወድጄ ፡ ፈቅጄ (Wedejie Feqejie) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

ወድጄ ፡ ፈቅጄ ፡ እኔ ፡ የማመልክህ
የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆነህ
እዚህ ፡ የመድረሻ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ

ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)

አንተን ፡ እያመለኩ ፡ ጉዞ ፡ ከጀመርኩኝ
በትንሹ ፡ ዕድሜዬ ፡ ቤትህ ፡ ከመጣሁኝ
ፍቅር ፡ እንጂ ፡ ከአንተ ፡ ክፉን ፡ አላየሁም
ለማምለክ ፡ ፈቅጄ ፡ በዚህ ፡ ተረታሁኝ

ተባረክ ፡ አሃሃ
ተመስገን ፡ ኦሆሆ (፪x)

በሕይወቴ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ
የምሰጠው ፡ ለአንተ ፡ ነው
በኑሮዬ ፡ ሰፊ ፡ ቦታ
የምሰጠው ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)

ጌታዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
አምላኬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ንጉሤ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ ነው

ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)

ፍቅር ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ ነህ (፪x)

ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)