ሰዎች ፡ እንዲፈርድብኝ (Sewoch Endiferdebegn) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ ሰዎች ፡ እንዲፈርድብኝ ፡ ጣሉኝ ፡ ከእግሩ ፡ ሥር
ትሙትልን ፡ አሉ ፡ በድንጋይ ፡ ትወገር
ያልጠበኩትን ፡ ቃል ፡ ጌታ ፡ ተናገረ
ኃጥያትን ፡ አትስሪ ፡ ምሬሻለሁ ፡ አለ

እኔማ ፡ አልታይም ፡ በባዶ ፡ እጆቼ
ይዤ ፡ መጥቻለሁ ፡ መላ ፡ እኔነቴን
ሁለንተናዬን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ
መሷቴን ፡ ይዤ ፡ በፊቱ ፡ እቀርባለሁ

አዝ፦ ሰዎች ፡ እንዲፈርድብኝ ፡ ጣሉኝ ፡ ከእግሩ ፡ ሥር
ትሙትልን ፡ አሉ ፡ በድንጋይ ፡ ትወገር
ያልጠበኩትን ፡ ቃል ፡ ጌታ ፡ ተናገረ
ኃጥያትን ፡ አትስሪ ፡ ምሬሻለሁ ፡ አለ

አትዎጭም ፡ እያሉ ፡ ሲዘባበቱብኝ
አምላኬ ፡ ዙፋን ፡ ስር ፡ እራሴን ፡ አዋረድኩኝ
በሮችን ፡ ከፋፍቶ ፡ መዝሙርን ፡ ሰጥቶኛል
ጠላትም ፡ እያየ ፡ እኔን ፡ አክብሮኛል

አዝ፦ ሰዎች ፡ እንዲፈርድብኝ ፡ ጣሉኝ ፡ ከእግሩ ፡ ሥር
ትሙትልን ፡ አሉ ፡ በድንጋይ ፡ ትወገር
ያልጠበኩትን ፡ ቃል ፡ ጌታ ፡ ተናገረ
ኃጥያትን ፡ አትስሪ ፡ ምሬሻለሁ ፡ አለ

አድርገህልኛል ፡ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ
ሥምህን ፡ ላሞጋግሰው ፡ በምድር ፡ በሠማይ
ከሕይወት ፡ እንጀራ ፡ እኔን ፡ አጥግበኸኛል
በመስቀል ፡ በመሞት ፡ ሕይወት ፡ ሆነኸኛል

አዝ፦ ሰዎች ፡ እንዲፈርድብኝ ፡ ጣሉኝ ፡ ከእግሩ ፡ ሥር
ትሙትልን ፡ አሉ ፡ በድንጋይ ፡ ትወገር
ያልጠበኩትን ፡ ቃል ፡ ጌታ ፡ ተናገረ
ኃጥያትን ፡ አትስሪ ፡ ምሬሻለሁ ፡ አለ