ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ (Menem Tarik Yelegn) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ ታሪኬም ፡ አንተ ፡ ነህ
ምንም ፡ ዝና ፡ የለኝ ፡ ዝናዬም ፡ አንተ ፡ ነህ
ምንም ፡ ክብር ፡ የለኝ ፡ ክብሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ነህ
ክብሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ነህ (፪x)

ታሪክን ፡ ለዋጭ ፡ ነህ ፡ ቀንበርን ፡ ሰባሪ
እስራትን ፡ ፈቺ ፡ ደግሞም ፡ ድል ፡ አድራጊ
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል
ሠማይ ፡ በምድር ፡ ብዞር ፡ የት ፡ ይመጣል

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ ራስህን ፡ ሰውተህ
ለበደል ፡ ለኃጥያቴ ፡ አንተ ፡ ቆስለህልኝ
ተውጬ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ
ሞትን ፡ ሞተህልኝ ፡ ብርሃን ፡ ለእኔ ፡ አበራ