ለአንተ ፡ መኖር (Lante Menor) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ
አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ
ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ
የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x)

ከአገር ፡ ከወገን ፡ ተለይቼ
ዘመድ ፡ አዝማድን ፡ ትቼ
ያልከኝን ፡ ሁሉ ፡ ሰምቼ
የገባህልኝ ፡ ተስፋ ፡ አይቼ

አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ
አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ
ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ
የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x)

አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ ፡ አላፈርኩም
ተናግረኸኝ ፡ መቼም ፡ አልከሰርኩም
በመንፈስህ ፡ ብርታት ፡ አግኝቼ
አመልክሃለሁ ፡ ተደስቼ

አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ
አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ
ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ
የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x)

ጌታ ፡ ሕይወቴን ፡ አደስከው
ተስፋዬን ፡ አለመለምከው
ማጉረምረሜን ፡ ከእኔ ፡ ወሰድከው
ሞቴንም ፡ በሕይወት ፡ ቀየርከው

አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ
አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ
ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ
የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x)