ጌታ ፡ ሰው ፡ አይጥልም (Gieta Sew Aytelem) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ የተረሳሁ ፡ ነበርኩ ፡ የተጣልኩኝ
በሰው ፡ ዘንድ ፡ ስፍራ ፡ ያልተሰጠኝ
ከዓለም ፡ ነፍሴን ፡ አወጣት
ጌታ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ አደረጋት

አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆንኩኝ ፡ በውዴ
መሰረቴም ፡ ጠብቋል ፡ የሕይወቴ
በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ዘለዓለም ፡ ኖራልሁ
ዕድሜዬን ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ

አዝ፦ የተረሳሁ ፡ ነበርኩ ፡ የተጣልኩኝ
በሰው ፡ ዘንድ ፡ ስፍራ ፡ ያልተሰጠኝ
ከዓለም ፡ ነፍሴን ፡ አወጣት
ጌታ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ አደረጋት

እኔ ፡ አወቀዋለሁ ፡ ሲያድነኝ
የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ ሲሆነኝ
በፍቅር ፡ እጆቹ ፡ ደግፎ
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ዘለዓለም ፡ ሊያኖረኝ

አዝ፦ የተረሳሁ ፡ ነበርኩ ፡ የተጣልኩኝ
በሰው ፡ ዘንድ ፡ ስፍራ ፡ ያልተሰጠኝ
ከዓለም ፡ ነፍሴን ፡ አወጣት
ጌታ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ አደረጋት

የዘለዓለም ፡ ባለውለታዬ
ከጠላቴ ፡ አዳነኝ ፡ ጌታዬ
ዘምርለታለሁኝ ፡ በደስታ
ኩራቴ ፡ እና ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጌታ

አዝ፦ የተረሳሁ ፡ ነበርኩ ፡ የተጣልኩኝ
በሰው ፡ ዘንድ ፡ ስፍራ ፡ ያልተሰጠኝ
ከዓለም ፡ ነፍሴን ፡ አወጣት
ጌታ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ አደረጋት

ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ከእርሱ ፡ ሆነልኝ
ሕይወቴን ፡ በእጆቹ ፡ ያዘልኝ
ሹመትን ፡ ሰጥቶኛል ፡ ኢየሱሴ
ሳልቆጥብ ፡ ላምልከው ፡ ጌታዬ

ጌታ ፡ ሰው ፡ አይጥልም (፬x)