ኧረ ፡ አመስግኑልኝ (Ere Amesgenulegn) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

ማህጸኗ ፡ ቢደርቅ ፡ . (1) . ፡ ይዟት
ተስፋዋ ፡ ተሟጦ ፡ ልጅ ፡ መውለድ ፡ ቢያቅታት
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ መቼ ፡ አረጀና
ይወለዳል ፡ ይስሃቅ ፡ እርሱ ፡ ብሏልና
(፪x)

አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x)

አብርሃም ፡ ቢያረጀም ፡ ሳራም ፡ ብትደካክም
ሁኔታውን ፡ አይተው ፡ የማይሆን ፡ ቢመስልም
ለጌታ ፡ ምን ፡ አቅቶት ፡ ምን ፡ ተስኖት ፡ ያውቃል
ይስሃቅን ፡ ሰጥቷቸው ፡ አስደንቋቸዋል
(፪x)

አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x)

የሚያስፈልግህን ፡ በጊዜው ፡ ያደርጋል
ታምነህ ፡ ከተቀመጥክ ፡ ቃሉንም ፡ ያከብራል
አድራሻህን ፡ አድርገው ፡ ከዙፋኑ ፡ ሥር
ፈጥኖ ፡ ይረዳሃል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
አድራሻሽን ፡ አድርጊው ፡ ከዙፋኑ ፡ ሥር
ፈጥኖ ፡ ይረዳሻል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር

አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን
እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን
ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x)