በሥሙ ፡ ታምኜ (Besemu Tamegnie) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም
(፪x)

ውድቀቴን ፡ ሲጠብቅ ፡ አሁንም ፡ ያ ፡ ክፉ
አታልፊውም ፡ ሲለኝ ፡ ቀኖቹም ፡ ሲከፉ
የነፍሴ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰና
እኔን ፡ አሻገረኝ ፡ ታሪክ ፡ ለወጠና

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም
(፪x)

ጠላት ፡ ሲያስለቅሰኝ ፡ ሸለቆ ፡ እያሳየ
እግዚአብሔር ፡ ከሠማይ ፡ ሰምቶ ፡ ዘንበል ፡ አለ
እንባዬን ፡ አብሶ ፡ ደስታን ፡ አለበሰኝ
ለልቤ ፡ መጽናናት ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ሆነልኝ

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም
(፪x)

ገበናዬን ፡ ሸፊኝ ፡ ሚስጥር ፡ ተካፋዬ
ጉድለቴን ፡ ሞላልኝ ፡ በእርሱ ፡ በጌታዬ
በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በመንፈስ ፡ ባርኮኛል
የመንግሥቱ ፡ ወራሽ ፡ ርስቱ ፡ አድርጐኛል

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም
(፪x)

ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አይቶ ፡ የሚራራ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና
ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ላብዛለት ፡ ምሥጋና
ክብር ፡ ያገኘሁት ፡ በአምላኬ ፡ ነውና

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም
ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም
(፪x)