በዓለም ፡ ተጥዬ (Bealem Teteyie) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

በዓለም ፡ ተጥዬ ፡ ዋጋም ፡ ሳይኖረኝ
በሰውም ፡ ተንቄ ፡ ስፍራንም ፡ ሳላገኝ
ቃሉን ፡ ሲያወጣ ፡ ከማደሪያው ፡ ቦታ
ታላቅም ፡ ሠራዊት ፡ አድርጐኛል ፡ ጌታ (፪x)

ሕይወቴን ፡ ሊጐዳ ፡ ዝቶብኝ ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ አዳነኝ ፡ ጥሶ ፡ ገብቶ ፡ ቤቴ
እኔም ፡ አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
አውጥቶኛልና ፡ ከጭንቅ ፡ ከመከራ

አዝየውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
(፪x)
ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል
ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ
እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ
ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ
ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ

አይተወኝም ፡ እርሱ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝም
በፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ገዝቶ ፡ ልቤን ፡ ማርኮ
አምነዋለሁ ፡ እርሱን ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው
አይጥለኝም ፡ ሁሌ ፡ ታማኝ ፡ ወዳጄ ፡ ነው

አዝየውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
(፪x)
ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል
ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ
እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ
ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ
ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ

ደግፎ ፡ ያቆመኝ ፡ እኔን ፡ በምህረት
የማውቀው ፡ ጌታን ፡ ነው ፡ ደግሞም ፡ በቸርነት
መጣ ፡ እኔንም ፡ አይቶ ፡ ያነሳኝ ፡ እርሱ ፡ ነው
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ነገ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ

አዝየውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
(፪x)
ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል
ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ
እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ
ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ
ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ