አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ (Amelkalehu Yehen Gieta) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ አመልከዋለሁ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሰግድለታለሁኝ ፡ በደስታ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ
ጌታዬን ፡ ልሾመው ፡ በሁለንተናዬ (፪x)

ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ መቼ ፡ ይተዋኛል
በብዙ ፡ ሰላሙ ፡ እርሱ ፡ ይመራኛል
የልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሁሉም ፡ በሚችለው
በዘለዓለም ፡ ኃይሉ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ

አዝ፦ አመልከዋለሁ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሰግድለታለሁኝ ፡ በደስታ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ
ጌታዬን ፡ ልሾመው ፡ በሁለንተናዬ (፪x)

በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ ብሆን ፡ በመከራ
በረከት ፡ ይሆናል ፡ በወሰንው ፡ ስፍራ
ሁሌ ፡ የምኮራበት ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ
የማምለጫ ፡ ዓለቴ ፡ መከታ ፡ ጋሻዬ

አዝ፦ አመልከዋለሁ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሰግድለታለሁኝ ፡ በደስታ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ
ጌታዬን ፡ ልሾመው ፡ በሁለንተናዬ (፪x)

አልደራደርም ፡ ከጠላቴ ፡ ጋራ
የቆመውም ፡ ችግር ፡ ቢሆንም ፡ በተራ
ልዩነት ፡ ይሆናል ፡ በአረማመዴ
ከቶም ፡ አይነካኝም ፡ አለና ፡ ጌታዬ

አዝ፦ አመልከዋለሁ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሰግድለታለሁኝ ፡ በደስታ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ
ጌታዬን ፡ ልሾመው ፡ በሁለንተናዬ (፪x)

እርሱን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌዋለሁ
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ በጥላው ፡ አድራለሁ
ዛሬ ፡ የሚታየውን ፡ ምድራዊው ፡ ችግሬ
እንዲህ ፡ አይቀጥልም ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አገሬ

አዝ፦ አመልከዋለሁ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሰግድለታለሁኝ ፡ በደስታ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ
ጌታዬን ፡ ልሾመው ፡ በሁለንተናዬ (፪x)