አለኝ ፡ የምለው (Alegn Yemelew) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ
አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ
አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር
መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x)

ቁስለኛውን ፡ ልቤን ፡ የሚጠግነው
የነፍሴን ፡ ህመም ፡ የሚፈውሰው
መንፈስህ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት
በምድር ፡ ያለውን ፡ አይደለም ፡ ያየሁት

የተሰበረውን ፡ አንተ ፡ የምትሻውን
መስዕዋት ፡ አድርገህ ፡ የምታሸተውን
ይህን ፡ መንፈስ ፡ ስጠኝ ፡ እለም
ጸሎቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ እለምንሃለሁ

አንተን ፡ የሚፈልግ ፡ ልብን ፡ ፍጠርልኝ
የቀናውን ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ አድስልኝ
ባክህን ፡ ጌታ ፡ ከፊትህ ፡ አትጣለኝ
ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ (፫x)

አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ
አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ
አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር
መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x)

መንገዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ያሳየኝ
የሕይወቴ ፡ መሪ ፡ ለእኔ ፡ የሆነልኝ
መንፈስህ ፡ ብቻ ፡ እረፍትን ፡ የሰጠኝ
ከመከራ ፡ ስጋት ፡ እኔን ፡ ያሳረፈኝ

ልክ ፡ እንደነኤልሳ ፡ እንደ ፡ ኤልያስ
ልቤ ፡ ታዛዥ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ መንፈስ
እንደ ፡ ወደድክ ፡ አርፈህ ፡ በእኔ ፡ እንድትሰራ
ሕይወቴን ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አደራ

ብርና ፡ ወርቅ ፡ ለእኔ ፡ ሰላም ፡ አልሆነኝም
ሃብትና ፡ ንብረትም ፡ እረፍት ፡ አልሰጠኝም
ውስጣዊው ፡ እርካታ ፡ የልቤ ፡ ደስታ
አንተ ፡ ነህ ፡ የሰጠኸኝ ፡ ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ክበር ፡ ክብር ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ
አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ
አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር
መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x)