አካሄዴን ፡ ጌታ (Akahiedien Gieta) - ኤልሳ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልሳ ፡ ጌታቸው
(Elsa Getachew)

Elsa Getachew 1.jpg


(1)

ያልጠበኩትን ፡ ቃል
(Yaltebekuten Kal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልሳ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Elsa Getachew)

አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና
ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና
ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው
እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x)

ከማር ፡ ከወለላ ፡ ሁሉ ፡ የሚጣፍጠው
ከነገሮች ፡ ሁሉ ፡ እጅጉን ፡ የሚበልጥ
አለኝ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ የተከበረው
ጌታም ፡ አጽንቶታትል ፡ የማይሻር ፡ ነው

አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና
ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና
ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው
እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x)

በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ አንተን ፡ እንዳመልክህ
ጌታ ፡ በኑሮዬ ፡ ቃልህን ፡ አብራልኝ
ከአመጸኛ ፡ ከንፈር ፡ ከሸንጋይ ፡ አንደበት
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጠብቀኝ ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ እንድኖር

አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና
ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና
ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው
እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x)

ባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ዝምም ፡ አትበለኝ
ቃልህን ፡ አብራልኝ ፡ ከፊትህ ፡ አትጣለኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቃልህ ፡ ተስፋ ፡ አደርገዋለሁ
በናፍቆት ፡ በጉጉት ፡ እጠባበቃለሁ

አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና
ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና
ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው
እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x)