Elias Gemechu/Saychelem/Saychelem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1.ልቤ ያዘነው በራሱ ነገር

አልሰማ ብሎ ጌታው ሲናገር

ይሄ ጎዳና አይጠቅምም አለው

ልቤ ደንድኖ አልሰማም አለው፥


ልቤ ተጎዳ በራሴ

አልሰማ ብዬው ኢየሱሴን

ሸክምህ ይቅለልልህ ሲለኝ

አልፈልግ ብዬ እኔ ሸሸሁኝ


አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

እረ አልመሸም ገና

እረ አልመሸም ገና

አሁንም ጊዜ አለ ተመለስ እንደገና

አልረፈደም ገና

አልረፈደም ገና

አሁንም ጊዜ አለ ተመለስ እንደገና


2.ንጉሡ ሳኦል ጌታው ሲያዘው

አንድም እንዳይቀር አጥፋልኝ ሲለው

ለራሱ ምኞት ተሸነፈና

ይዞአቸው መጣ ማጥፋት ተወና


ቢደርስህ የ ንግሥ እጣ

አንተ ግን ከሀሳቡ ወጣህ

ከ ሳኦል አትማርም ወይ

የተጳፈው ላንተ አይደለም ወይ ?


አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

እረ አልመሸም ገና


3.ሙሽራውን ሊቀበሉ ወተው

ዘይት ትርፍ ይዘው ብርሀን ለኩሠው

ሲጠባበቁ ይመጣል እያሉ

በተስፋ ቆመው ፍፁም ሳይደክሙ


ሰነፍቹ ተዘናግተዋል

ዘይቱም ነዶ አልቆባቸዋል

ሙሽራው መቶ በሩን ዘጋው

በ እውንት አላውቃችሁም ።


አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

እረ አልመሸም ገና፣


4.ሳይጨላልም ቶሎ ተመለስ

ምህረት ለምነህ በጊዜ ድረስ

ኃላ ካለፈ መመለሻህ

ሞት እንዳይመጣ እንዳይቀድምህ

ቀጠሮ አትስጠው ቶሎ ና

አምላክህ ይጠራሀል እና

የ አለም ዝናዋ ይቅርብህ

የ ዘላለም ህይወት ይብለጥብህ


አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠


እረ አልመሸም ገና፣