ፍቅር ፡ ያሸንፋል (Feqer Yashenefal) - ኤልያስ ፡ ገመቹ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልያስ ፡ ገመቹ
(Elias Gemechu)

Elias Gemechu 1.jpg


(1)

ሳይጨልም
(Saychelem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ ገመቹ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Gemechu)

አዝ፦ ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ አቤት
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ እህ
ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ

በፍቅር ፡ ተገዶ ፡ ጌታዬ ፡ ሲመጣ
ምህረት ፡ ሊያደርግልን ፡ ከኃጢአት ፡ ሊያወጣ
ጠላቶቹን ፡ ወዶ ፡ ለወጉት ፡ ሲሞት
ሊያሳየን ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ የፍቅሩን ፡ ጥልቀት

ሄሄሄ ፡ ለወጉት ፡ ሲሞት
ሆሆሆ ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ብሎት (፪x)

አዝ፦ ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ አቤት
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ እህ
ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ

ፍቅር ፡ አሸንፏል ፡ እሜን
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ አሜን
ኢየሱስ ፡ አሸንፏል ፡ አሜን
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ አሜን

ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ከአስፈሪው ፡ ሌሊት
ሊያወጣን ፡ ሲመጣ ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ብሎት
ጠላቶቹ ፡ ሳለን ፡ ወዳጅ ፡ አድርጐን
ብርሃናችን ፡ በራ ፡ ምህረቱን ፡ ሰጥቶን

ሄሄሄ ፡ ጠላቶቹ ፡ ሳለን
ሆሆሆ ፡ ወዳጅ ፡ አድርጐን
ሄሄሄ ፡ ከውድቅቱ ፡ ሌሊት ፡
ሆሆሆ ፡ በፍቅሩ ፡ አወጣን

አዝ፦ ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ አቤት
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ እህ
ፍቅር ፡ ያሸንፋል ፡ አዎ
ምህረትን ፡ ያደርጋል ፡ እህ

ፍቅር ፡ አሸንፏል ፡ እሜን
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ አሜን
ኢየሱስ ፡ አሸንፏል ፡ አሜን
ዓይናችን ፡ አይቶታል ፡ አሜን

በፍቅሩ ፡ የረታን ፡ ኢየሱስ ፡ ይሸነፈን
ለምድራዊው ፡ ክብር ፡ አይደለም ፡ የጠራን
መጽሐፉ ፡ ምን ፡ ይላል ፡ እውነትን ፡ ገላጩ
በክብር ፡ እንሄዳለን ፡ ነንና ፡ ሌጆቹ

ሄሄሄ ፡ ብሎ ፡ ጠርቶናል
ሆሆሆ ፡ ሰማያዊ ፡ ዜጐች
ሄሄሄ ፡ የመንግሥትን ፡ ሰማይ
ሆሆሆ ፡ የክብር ፡ ወራስሾች

ለፍቅሩ ፡ ውለታ ፡ ምን ፡ እመልሳለሁ
የተደረገልኝ ፡ ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
በዕልልታ ፡ በሆታ ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ
የተደረገልኝ ፡ ከእዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው

ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ጌታ ፡ ያደረገው ፡ ከእዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (፭x)