በቃ (Beqa) - ኤልያስ ፡ ገመቹ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤልያስ ፡ ገመቹ
(Elias Gemechu)

Elias Gemechu 1.jpg


(1)

ሳይጨልም
(Saychelem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ ገመቹ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Gemechu)

አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ
ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ
በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ ቀይሮ

በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ
ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ
በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x)

ሰላሳ ፡ ስምንት ፡ አመት
በአልጋዬ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ ተኝቼ (ኦሆ ፡ ኦሆ)
መልዓኩ ፡ ሲያናውጠው
ወደ ፡ ውሃው ፡ ሚከተኝ ፡ አጥቼ (ኦሆ ፡ ኦሆ)

አቅም ፡ የለኝ ፡ ወገን ፡ የለኝ
ውስጤ ፡ እያለ ፡ ተማረረ (ኦሆ ፡ ኦሆ)
እምባ ፡ ቀደሙት ፡ ዓይኖቼ
ልቤም ፡ እጅጉን ፡ አዘነ

አበቃልኝ ፡ በቃ ፡ ዛሬ
ሊቀጥል ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ህመሜ
ብዬ ፡ ሳስብ ፡ በትካዜ
ጌታ ፡ ቆሟል ፡ ከአጠገቤ (፪x)

አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ
ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ
በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x)

ጨለማ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ኑሮ
ብርሃን ፡ አጥቶ ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ (ኦሆ ፡ ኦሆ)
ወጣሁ ፡ ምጽዋትን ፡ ጥየቃ
እንደድሮ ፡ እንደወትሮ (ኦሆ ፡ ኦሆ)

ምንድነው ፡ ኢሄ ፡ ጩኸቱ
ብዬ ፡ ጠየኩ ፡ የሚያልፍ ፡ ሰው (ኦሆ ፡ ኦሆ)
ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ መጥቶ ፡ ነው
ፈዋሹ ፡ እያለፈ ፡ ነው

የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ማረኝ ፡ ብዬ
አላለፍከኝ ፡ አባብዬ
ፊትህንም ፡ አዞርክልኝ
ጨለማዬን ፡ ገፈፍክልኝ (፪x)

አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ
ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ
በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x)

ምንድነው ፡ እርሱ ፡ በዛብኝ
ችግርና ፡ መከራዬ (ኦሆ ፡ ኦሆ)
የሞት ፡ ጥላ ፡ አጠላብኝ
አታየኝም ፡ ወይ ፡ ጌታዬ (ኦሆ ፡ ኦሆ)

ከአባቶቼ ፡ እንደተማርኩት
ከቃልህ ፡ እንዳነበብኩት (ኦሆ ፡ ኦሆ)
ጩኸት ፡ ሰምተህ ፡ መልሰሃል
ለስንቱ ፡ ሕይወት ፡ ሆነሃል

የእኔስ ፡ ቀን ፡ መቼ ፡ ነው ፡ አልኩኝ
ተንበርክኬ ፡ ተማጸንኩኝ
ጸሎቴም ፡ ተሰማልኝ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በቃህ ፡ አለኝ (፪x)

በቃ ፡ በቃ ፡ በቃ
በቃ ፡ በቃ ፡ በቃ
የሰቆቃው ፡ ዘመን
ከእኔ ፡ ላይ ፡ አበቃ (፬x)