ቅባትህ (Qebateh) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(?)

ያልታወቀ ፡ አልበም
(Unknown Album)

ቁጥር (Track):

()


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

አዝ፦ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ ፡ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
በኢያሪኮ ፡ መንገድ ፡ ለወደቀው ፡ እንድደርስ
የኤልዛቤልን ፡ ግልሙትና ፡ እንዳፈርስ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
የተሰወረውን ፡ የጠላት ፡ አመጽ ፡ ይምታ

ዘይት ፡ እንደሌላቸው ፡ ሌዋዊና ፡ ካህን
ቁስለኛውን ፡ እያዩ ፡ እንዳላዩ ፡ የሚያልፉትን
መሆን ፡ አልፈልግም ፡ በጎነት ፡ የሌለው
ቅባትህ ፡ ይምጣና ፡ ያንን ፡ ሰው ፡ ልታደገው

አዝ፦ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ ፡ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
በኢያሪኮ ፡ መንገድ ፡ ለወደቀው ፡ እንድደርስ
የኤልዛቤልን ፡ ግልሙትና ፡ እንዳፈርስ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
የተሰወረውን ፡ የጠላት ፡ አመጽ ፡ ይምታ

በዝሙቷ ፡ ጉልበት ፡ ጎበዞችን ፡ የጣለች
የእስራኤልን ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያስካደች
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ትሴስን ፡ ትቀመጥ
ልበቀላት ፡ ጌታ ፡ ቀባኝ ፡ ኤልዛቤል ፡ ትገልበጥ

አዝ፦ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ ፡ ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
በኢያሪኮ ፡ መንገድ ፡ ለወደቀው ፡ እንድደርስ
የኤልዛቤልን ፡ ግልሙትና ፡ እንዳፈርስ
ቅባትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ በእጥፍ ፡ ይምጣ
የተሰወረውን ፡ የጠላት ፡ አመጽ ፡ ይምታ

በእግዚአብሔር ፡ ዕውቀት ፡ ላይ ፡ ከፍቶ ፡ የተነሳ
የክንድህን ፡ ብርታት ፡ ክርስቶስን ፡ ሚያስረሳ
በስምህ ፡ መጽናቴን ፡ ጠላት ፡ አሁን ፡ ይወቅ
አሳቡን ፡ አልስትም ፡ እዋጋለሁኝ ፡ ይውደቅ