From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ
ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ
የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ
ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ
ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ
የነገስታትን ፡ ኩራት ፡ ባዶ ፡ ያረገ
ለምስኪኖች ፡ መንገሻ ፡ መንገድ ፡ ጠረገ
የዚህችን ፡ አለም ፡ ጥበብ ፡ ለማሳፈር
እኛን ፡ ሞኞች ፡ መረጠ ፡ ዘላለም ፡ ይክበር
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ
ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ
የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ
ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ
ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ
ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ታጠቀ
ጉስቁልናን ፡ ከልጆቹ ፡ አራቀ
አኖቹ ፡ እንደ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ናቸው
ጨለማን ፡ ያስወገደ ፡ ክብሩን ፡ ታላቅ ፡ ነው
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ
ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ
የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ
ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ
ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ
ከሰማይ ፡ በአመጻው ፡ የተወለደ
በምድርም ፡ በሰዎች ፡ ላይ ፡ ሞት ፡ ያወረደ
ኢየሱስ ፡ ከላይ ፡ ሲገለጥ ፡ የእኛ ፡ አባባ
ጠላት ፡ የለም ፡ የታለ ፡ የት ፡ ፡ እንደ ፡ ገባ
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ
ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ
የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ
ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ
ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ
በአራቱም ፡ ማዕዘናት ፡ ክብሩ ፡ እያበራ
ውዳችን ፡ ይገለጣል ፡ ከመላዕክት ፡ ጋራ
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ስንሻገር ፡ ከአድማስ ፡ ወዲያ
ተስፋችን ፡ ይፈጸማል ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ
ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ
የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ
ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ
ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ
|