From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ
የህይወቴ ከለላ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተመስገን ሃሌሉያ
በህይወቴ የሞላው የሃጥያት ነቀርሳ
ለሞት እስኪያስጨንቅ እጅጉን ሲበዛ
የጣር ጩኸቴን ሰምቶ ከሰማይ ወረደ
ነፍሴን ሰላም ሰጣት ሞቴን አስወገደ
የማይገባኝን ሰማያዊ ጥሪ
የጠራኝ ሳያንሰው አረገኝ መስካሪ
የምህረቱን ብዛት በነፍሴ አሳየኝ
በህይወት ስላኖረኝ ክብርን እሰዋለሁኝ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ
የህይወቴ ከለላ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተባረክ ሃሌሉያ
በበረታ ሃዘን መንፈሴ ተሰብሮ
መጽናናት ሲርቀኝ ዘመናትን ቆጥሮ
በድካም በዝለት በወደኩት ስፍራ
ውዴ ኢየሱስ መጣ በስሜ ተጣራ
እንባዬን አበሰ አይኖቼን ከፈተ
ለደቀቀው ልቤ መጽናናትን ሰጠ
እንደርሱ ሚሆነኝ አላገኘሁምና
በፊቱ እሰዋለሁ ለስሙ ምስጋና
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ
የህይወቴ ከለላ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተባረክ ሃሌሉያ
ቁስሌን በዘይት ስታሽ ድርቀቴን ስትፈውስ
ስብራቴን ስትጠግን አንባዬን ስታብስ
ጠያቂዎቼ ብዙ አስታማሚዎቼ
ከኔ እንደማይሻሉ አየሁኝ በአይኖቼ
መጽናናት ሃይልንም ከእኔ ጠበቁ
ከአፌ በወጣው ቃል ተፈውሰው ሳቁ
ክብሬም ታድሶልኝ በትሬም ለምልሞ
ደስታዬን ለማየት ሰዉ ተሽቀዳድሞ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ
የህይወቴ ከለላ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተባረክ ሃሌሉያ
ብላቴናነቴ ተንቆ ወንጭፌ
ከጎልያድ አንደበት እርግማን ጠግቤ
ቅናቱ ሲበላኝ የስምህ መሰደብ
ፈተና ሆኖ ፊቴ በእንባ ሲታጠብ
በእኔ ላይ የአለው የመንፈስህ ብርታት
በክቡር ስምህ ስልጣን ጉልበትህ ሲገለጥ
ያነሳሁት ድንጋይ መቼ የዋዛ ሆነ
ጠላቴን አድቅቆ ስምህን አስከበረ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ
የህይወቴ ከለላ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተባረክ ሃሌሉያ
ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ
ተመስገን ሃሌሉያ
|