From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት
ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት
እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው
በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው
ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
በጎነቱ ፡ ሲነገረኝ ፡ ማዳኑ ፡ መቼ ፡ ማረከኝ
ጆሮዬን ፡ በእጄ ፡ ዘግቼ ፡ ኢየሱስን ፡ አይን ፡ ላፈር ፡ አልኩኝ
መራቡን ፡ ያላወቀ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ እንጀራ ፡ አንስቶ ፡ ይብላ
ኋላ ፡ ግን ፡ ሲሞረሙረው ፡ ይሻዋል ፡ ቀድሞ ፡ እንዳልበላ
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት
ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት
እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው
በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው
ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
መስቀሉን ፡ በጀርባው ፡ ጭኜ
ጦሬን ፡ መዝዤ ፡ ጨክኜ
ጎልጎታ ፡ ድረስ ፡ ወሰድኩት
እጁን ፡ ቸንክሬ ፡ ሰቀልኩት
ከአዘነለት ፡ ሰው ፡ ይልቅ ፡ ምህረቱ ፡ ለኔ ፡ ቀደመ
ሚያደርገውን ፡ አያውቅምና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረው ፡ ተባለ
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት
ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት
እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው
በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው
ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
ኃጢያቴ ፡ በዝቶ ፡ በደጄ ፡ ሊገድለኝ ፡ ሲጥር ፡ ሲያደባ
ባፈሰስኩበት ፡ ደሙ ፡ አጥቦ ፡ ሊያነፃኝ ፡ ቃል ፡ ገባ
አጥንቴ ፡ ደቆ ፡ ስቆዝም ፡ አይዞህ ፡ የሚል ፡ ሰው ፡ ሲጠፋ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ደረሰ ፡ ያኔ ፡ በእጄ ፡ የተገፋ
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት
ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት
እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው
በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው
ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
አጥላልቼው ፡ ከወደደ ፡ ለሰቀልኩት ፡ ከማለደ
ምን ፡ ይሆንለት ፡ ምላሹ ፡ እንደ ፡ ስራዬ ፡ ካላዋረደኝ
ኢየሱሴ ፡ አድነኝ ፡ ስለው ፡ ያኔ ፡ ምን ፡ አረክ ፡ አላለም
እንደ ፡ እርሱ ፡ ትሁት ፡ ቸር ፡ የለም ፡ ስሙ ፡ ይባረክ ፡ ዘላለም
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት
ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት
እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው
በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው
ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
ኃጢያቴን ፡ ያልቆጠረብኝ
ምህረቱን ፡ ያበዛልኝ
ቸርነቱን ፡ ያወረደው ፡ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ
|