From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ከእኔ ከእሾሃማው ግራር እንጨት
ለቃልህ ማደሪያ ታቦት መስራት
ምንኛ ብትወደኝ ይህን አሰብክ
ታላቅ ውለታህን በእኔ ፈጸምክ
ስትቀርፀኝ ጣትህን አየች አይኔ
ተመስገን መድህኔ
እሾሄ ተራግፎ መቀመጫህ ሲለሰልስ
በልቤ ዙፋን ተቀምጠህ ስትነግስ
የእሾሁ ገበሬ ፊቱ ጠቁሮ ተናደደ
የድካሙ ዋጋ ሳያገኘው ሲዖል ሄደ
ከእኔ ከእሾሃማው ግራር እንጨት
ለቃልህ ማደሪያ ታቦት መስራት
ምንኛ ብትወደኝ ይህን አሰብክ
ታላቅ ውለታህን በእኔ ፈጸምክ
ስትቀርፀኝ ጣትህን አየች አይኔ
ተመስገን መድህኔ
በጨለመው ልቤ ተንሰራፍተህ ስትቀመጥ
አሮጌ ኑሮዬን በአንድ ጊዜ ስትለዋውጥ
እግሬም ተራመደ በህይወቴ ብርሃን በራ
ቀድሞ ያጨለመኝ ያ ጠላቴ ሊያየኝ ፈራ
ከእኔ ከእሾሃማው ግራር እንጨት
ለቃልህ ማደሪያ ታቦት መስራት
ምንኛ ብትወደኝ ይህን አሰብክ
ታላቅ ውለታህን በእኔ ፈጸምክ
ስትቀርፀኝ ጣትህን አየች አይኔ
ተመስገን መድህኔ
ለማይታሰብ ፍጡር የእርግማን ዛፍ የነበርኩኝ
ዛሬ በምህረት ህ ለማደሪያህ ተመረጥኩኝ
እንዲህ ከወደድከኝ እሾሄንም ካራገፍከው
የምለው የለኝም ክቡር ስምህን አከብራለሁ
ከእኔ ከእሾሃማው ግራር እንጨት
ለቃልህ ማደሪያ ታቦት መስራት
ምንኛ ብትወደኝ ይህን አሰብክ
ታላቅ ውለታህን በእኔ ፈጸምክ
ስትቀርፀኝ ጣትህን አየች አይኔ
ተመስገን መድህኔ
የከነረው መዝገብ በሸክላው ውስጥ አስቀመጥከው
ተናዳፊውን ሰዉ የክብር ቤት አደረከው
አይኖችህ ከአርያም ወደ ምድር ሲጎበኙ
ተመስገን ኢየሱሴ እኔን ከጉድጓድ አገኙ
ከእኔ ከእሾሃማው ግራር እንጨት
ለቃልህ ማደሪያ ታቦት መስራት
ምንኛ ብትወደኝ ይህን አሰብክ
ታላቅ ውለታህን በእኔ ፈጸምክ
ስትቀርፀኝ ጣትህን አየች አይኔ
ተመስገን መድህኔ
|