ክብርን ፡ እንሰጣለን (Keberen Ensetalen) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(1)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም
(Yemitesewen Tuafien Alatefam)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

ሰማይ ፡ ዝፋንህ ፡ ነው ፡ መቀመጫህ
ምድርም ፡ ለእግሮችህ ፡ መርገጫህ
ለትልቅነትህ ፡ ወሰን ፡ ነህ ፡ የሌለህ
ሰማያትንም ፡ በስንዝር ፡ የለካህ
እንሰግዳለን ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ጌታ

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

እስትንፋሽን ፡ ለሙታን ፡ ትሠጣለህ
በባዶ ፡ ሸለቆ ፡ ውሃን ፡ ትሞላለህ
ጥበብህን ፡ ችሎታህን ፡ ማን ፡ ይለካዋል
ያልነበርን ፡ እንደምታኖር ፡ አውቀዋል
ከፍ ፡ ያልከው ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

እንዲበላ ፡ እንዲጠጣ ፡ ለራሱ ፡ እንዲኖር
ብቻ ፡ አልነበርም ፡ ሰውን ፡ በእጅህ ፡ መስራት
እንዲያመልክህ ፡ በታላቅነት ፡ እንዲያከብርህ
መሆኑን ፡ ተረድቻለሁ ፡ እኔን ፡ መፍጠርህ
ታላቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን