ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን (Hayleh Bezu Sihon) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(1)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም
(Yemitesewen Tuafien Alatefam)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ
የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ
ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ

ያ ፡ አስፈሪው ፡ ግርማህ ፡ ለአንዳፍታ ፡ ተቀይሮ
ጌታነትህ ፡ ክብር ፡ በባርነት ፡ ተመንዝሮ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከሆንክ ፡ አራስህን ፡ አድን ፡ ሲሉህ
የእኔን ፡ ቂም ፡ በእንተ ፡ በመስቀል ፡ ሲወጡ
ነፍሴ ፡ ወጣች ፡ ከእስራቱ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ
የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ
ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ

የሰው ፡ አንቆቅልሽ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ምላሽ ፡ ሲያገኝ
ለተገፊዎቹም ፡ ችሎት ፡ ቀርበህ ፡ ስትል ፡ ይግባኝ
በአንተ ፡ መገፋት ፡ ግን ፡ ሰማይ ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ሲሉ
ሃይልህ ፡ አስኪገለጥ ፡ አጅግ ፡ ቢያቃልሉህ
በክንድህ ፡ ሲዖል ፡ ተጣሉ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ
የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ
ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ

የክፋቴ ፡ ብዛት ፡ በሰው ፡ አፍ ፡ መርገም ፡ ሆኖ
ወሬ ፡ ለሚሰማ ፡ ለሚያይም ፡ አይን ፡ አስጨፍኖ
በሰፈሬ ፡ ስታልፍ ፡ ያንን ፡ ስድቤን ፡ ስትሸከም
በቁጣው ፡ ስትደርቅ ፡ ነፍሴን ፡ ለማለምለም
ከፍ ፡ በል ፡ ለዘለዓለም

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ
የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ
ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ

ቆሞ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ከህያዋን ፡ መቀላቀል
በሚመጣውም ፡ አለም ፡ ብቤትህ ፡ አኔን ፡ ስትቀበል
ከዚያም ፡ አልፎ ፡ የጓዳዬ ፡ መከራ ፡ ሲረሳ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ቀረ ፡ ያ ፡ አበሳ
ክበር ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ
የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ
ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ