ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ (Hayleh Bedekamie Sigelet) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(1)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም
(Yemitesewen Tuafien Alatefam)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ከባርነት ፡ ቤት ፡ ስታላቅቀኝ
ቀንበሬን ፡ ሰብረህ ፡ ስትጥልልኝ
ባህሩን ፡ በክንድህ ፡ ስትከፍልልኝ
ጭቃው ፡ ሳይነካኝ ፡ ስታሻግረኝ
ጫማዬ ፡ አልቆ ፡ በእግሬ ፡ ሳልሄድ
ጨርቄም ፡ ከገላዬ ፡ ሳይቀደድ
በበለዓም ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ለድንኳኔ
አጎናጸፍከኝ ፡ ክበር ፡ መድህኔ
ንገሥ ፡ መድህኔ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ቆሜያለሁ ፡ ሚልን ፡ የሚያፍገመግም
ብርቱ ፡ ነኝ ፡ ያለውን ፡ የሚያደክም
ይሄ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ፍጹም ፡ ሲያሯሩጥ
በወዳጁ ፡ ፊት ፡ ሲያለማምጥ
ክረምትም ፡ በጋም ፡ ለማይሞላው ፡ ሆድ
ሗላውን ፡ ሳያውቅ ፡ ሰው ፡ ሲካካድ
ሁሉን ፡ አራግፋ ፡ ያየችህ ፡ ነፍሴን
በድንቅ ፡ አኖርካት ፡ ክበር ፡ ኢየሱሴ ፡ ንገስ ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ጉስቁልናዬን ፡ እያስቆጠረኝ
ይሄ ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስለቅሰኝ
የቀራዮን ፡ ደም ፡ አንዳልዘነጋ
አይኔን ፡ አቅንቼ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ
ጉስቁልናዬን ፡ በብልጽግና
ከላይ ፡ ከአርያም ፡ ሞላህና
ስት ፡ ሸላልመኝ ፡ እፍረት ፡ ሆነለት
አበሳውንም ፡ አበዛህበት
ጠላቴን ፡ ክበር ፡ የኔ ፡ አባት

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

በአንዳንዱ ፡ ቀን ፡ ውስጤን ፡ ሲከፋው
የነፍሴን ፡ ጓዳ ፡ ባዶ ፡ ነህ ፡ ሲለው
መታጠቂያዬን ፡ ማጥበቅ ፡ ሲያቅተኝ
ታናሽነቴ ፡ ሚናቅ ፡ ሲመስለኝ
ደመናን ፡ ቀዶ ፡ ክንድህ ፡ ይወርዳል
መወርወሪያውን ፡ ይቆራርጣል
ሥራዬን ፡ ሰርተህ ፡ ስትዋጋልኝ
እጆቼን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አስጫንከኝ
ተመስገንልኝ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ