ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ (Bieteh Betesera Gizie) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(1)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም
(Yemitiesewen Tuafen Alatefam)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም
መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ
ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ
በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ
አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ

ድንጋዩ ፡ እንዳይታይ ፡ በዝግባ ፡ ሲለበጥ
ዝግባው ፡ ባማረ ፡ ወርቅ ፡ ሲያጌጥ
መስራትም ፡ መሰራትም ፡ ያኔ ፡ ነበረ
ይታያልም ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ
ድንጋይ ፡ በድንጋይ ፡ ላይ ፡ ይፈርሳ ፡ ተባለ
መች ፡ ቀረ ፡ ይኸው ፡ አሁን ፡ ሆነ
ወንድም ፡ ከወንድሙ ፡ ጋራ ፡ ሳይጣበቅ ፡
በጩኸት ፡ ሞቀ ፡ ቤቱ ፡ ጋለ

አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም
መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ
ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ
በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ
አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ

ዘሩ ፡ በመንገድ ፡ ዳር ፡ ወድቆ ፡ ሲለቀም
በጭንጫ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ ሲከስም
ግማሹ ፡ በእሾህ ፡ መሃል ፡ ሲታነቅ
ባለ ፡ ፍሬ ፡ ጠፍቶ ፡ ሲደርቅ
ከወርቅ ፡ ይልቅ ፡ የሚፈተነው ፡ እምነት ፡ በዝማሬ ፡ ተመስሎ ፡ ጠፋ
ከነኣን ፡ ላይገባ ፡ በኢያሪኮ ፡ ዙሪያ ፡ ሞልቷል ፡ መለከት ፡ የሚነፋ

አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም
መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ
ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ
በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ
አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ

እርስ ፡ በእርሳቸው ፡ የማይገላመጡ
ለእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ሚሮጡ
አገልጋዮች ፡ የሉም ፡ ራሳቸውን ፡ የካዱ ፡ ማይነቀፉ ፡ የተለወጡ
ፍርድን ፡ ከራሱ ፡ ቤት ፡ ይጀምራልና ፡
ወደ ፡ ህያው ፡ ድንጋይ ፡ እናቅና
በታቦት ፡ ብቻ ፡ እልልታን ፡ ከማቅለጥ
ኢየሱስን ፡ እንምሰል ፡ እንደግ

አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም
መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ
ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ
በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ
አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ
ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ