From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ
የሕይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ
በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ
ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ
ለአብርሃም አከብርሃለሁ
ዘርህን አበዛለሁ
ብለህ በተስፋ ስትጠራው
ዘሩን ልታበዛው
ተስፋው ሲዘገይ ከሳራ ጋር አብሮ ተማከረ
እርጅናው ሲዘምር ከተስፋው ቃል ጥቂት ፈቀቅ አለ
አብርሃም ቢያረጅ አታረጅም
ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም
እንደተናገርክ ታደርጋለህ
ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትኖራለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትሰራለህ
ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ
የህይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ
በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ
ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ
በሕይወት በኑሮ ጌታዬ ሆይ እጅግ ደክሜያለሁ
ፍሬ ሳይኖረኝ ዘመናትን ብዙ አሳልፌያለሁ
ሃይሌ አልቆብኝ ጉልበቶቼ እየተብረከረኩ
አለኝ ያልኩትን የያዝኩትን ከእጄ ተማረኩ
እኔ ባረጅ አታረጅም
ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም
ሕይወቴን አንተ ታድሳለህ
ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትኖራለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትሰራለህ
ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ
የሕይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ
በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ
ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ
እምነቴ በፊትህ እጅግ ደክሞ ውስጤ ባዶ ሆኗል
ወደ አንተ የሚያራምደኝ ብርታቱ ጠፍሮኛል
የቀድሞውን ብርቱነቴን ዓይኔ ማየት ናፍቃ
ነፍሴ ጎብኘኝ ትልሃለች ፊትህ ተንበርክካ
እኔ ባረጅ አታረጅም
ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም
ሕይወቴን አንተ ታድሳለህ
ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትኖራለህ
ጥንትም ብርቱ ነህ
ዛሬም ብርቱ ነህ
ነገም ትሰራለህ
እምነቴ በፊትህ እጅግ ደክሞ ውስጤ ባዶ ሆኗል
ወደ አንተ የሚያራምደኝ ብርታቱ ጠፍሮኛል
የቀድሞውን ብርቱነቴን ዓይኔ ማየት ናፍቃ
ነፍሴ ጎብኘኝ ትልሃለች ፊትህ ተንበርክካ
|