ወጉ ፡ ነው ፡ መመለክ (Wegu New Memelek) - ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ
(Edom Leulseged)

Edom Leulseged 1.jpg


(1)

አንተ ፡ ገናና
(Ante Genana)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤዶም ፡ ልዑልሰገድ ፡ አልበሞች
(Albums by Edom Leulseged)

ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ
ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው?
አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው!

የምድርን ፡ መሠረት ፡ ያጸና
መስፈሪያ ፡ መለኪያዋን ፡ የዘረጋ
ከእግዚአብሕዔር ፡ ሌላ ፡ ኧረ ፡ ማነው?
ሊመለክ ፡ ሊከበር ፡ የሚገባው!

በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ምሥጋናውን
በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ዝማሬውን
በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ አምልኮውን
እጅጉን ፡ የከበረውን ፡ የከበረውን
መልሼ ፡ አከብረዋለሁን ፡ አከብረዋለሁኝ
እጅጉን ፡ የገነነውን ፡ የገነነውን!
መልሼ ፡ አገነዋለሁኝ ፡ አገነዋለሁኝ!

ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ
ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው?
አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው!

ሰማይ ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ የጸና
ምድር ፡ ደግሞ ፡ የእግርህ ፡ መረገጫ
በዓይነቱ ፡ በፍጥረቱ ፡ የሚያስደንቅ
እግዚአብሔር ፡ ሆነብኝ ፡ ለእኔስ ፡ ትልቅ

ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ
ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው?
አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው!

ብቻውን ፡ አዛዥ ፡ ነው ፡ አጋዥ ፡ ሳይሻ
ትዕዛዙንስ ፡ የሚሽር ፡ የቱ ፡ ጀግና ?
ያለ ፡ ተቀናቃኝ ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛ
አልፋና ፡ ዖሜጋ ፡ ነው ፡ ጌታ !

በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ምሥጋናውን
በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ዝማሬውን
በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ አምልኮውን
እጅጉን ፡ የከበረውን ፡ የከበረውን
መልሼ ፡ አከብረዋለሁን ፡ አከብረዋለሁኝ
እጅጉን ፡ የገነነውን ፡ የገነነውን !
መልሼ ፡ አገነዋለሁኝ ፡ አገነዋለሁኝ !

ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ
ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው?
አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው!