ዋናዬ ፡ ኢየሱስ (Wanayie Eyesus) - ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ
(Edom Leulseged)

Edom Leulseged 1.jpg


(1)

አንተ ፡ ገናና
(Ante Genana)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤዶም ፡ ልዑልሰገድ ፡ አልበሞች
(Albums by Edom Leulseged)

አዝ ፣ኢየሱስ ፡ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x)
እኔ ፡ የማመልከው ፡ አንድ ፡ ነው
ስሙም ፡ ኢየሱስ (፬x)

አልችልበትም ፡ ለሌላ ፡ መስገድ
እኔ ፡ ማመልከው ፡ አንድ ፡ ነው
ስሙም ፡ ኢየሱስ (፪x)

አንድ ፡ ሁለት ፡ ብል ፡ ሶስተኛ ፡ አራተኛ
ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ምዕራፍ ፡ መጀመሪያ
እረፍቴ ፡ ሰላሙ ፡ ቤቴን ፡ ሞላ
ቃል ፡ ገባሁኝ ፡ ላላመልክ ፡ ከሱ ፡ ሌላ
መውደዱ ፡ ቤቴ ፡ አቆመኝ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሉን ፡ አስጣለኝ (፪x)
የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ዋናዬ ፡ እርሱ ፡ ነው (፬x)

አዝ ፣ኢየሱስ ፡ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x)
እኔ ፡ የማመልከው ፡ አንድ ፡ ነው
ስሙም ፡ ኢየሱስ (፬x)

እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ ተማረክሁለት
ጠቅልሎ ፡ ሊገዛው ፡ የእኔን ፡ ማንነት
ሁሉ ፡ ይቅር ፡ ምንም ፡ ከሱ ፡ አይበልጥም
መሻቴ ፡ ይኸ ፡ ነው ፡ ጌታን ፡ ማስቀደም
መውደዱ ፡ ቤቱ ፡ አቆመኝ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሉን ፡ አስጣለዝኝ
የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ዋናዬ ፡ እርሱ ፡ ነው

አዝ ፣ኢየሱስ ፡ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x)
እኔ ፡ የማመልከው ፡ አንድ ፡ ነው
ስሙም ፡ ኢየሱስ (፬x)