From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ
እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ
ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x)
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄ
ልልህ ፡ እወዳለሁ ፡ ባለችኝ ፡ ቋንቋዬ ፡ (አቅሜ)
ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ ተመስግኖ ፡ ኖሯል
ዓለምም ፡ ተፈጥሮ ፡ እስካሁን ፡ ተመልኳል
ትልቁም ፡ ትንሹም ፡ ገናና ፡ ብሎታል
እኔም ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ ያንኑ ፡ ልደጋግም
አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ
እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ
ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x)
ፍልስፍና ፡ በዝቶ ፡ ዕውቀት ፡ ተከማችቶ
ጥበብ ፡ በጥበብ ፡ ላይ ፡ ሲታይ ፡ ተደርቦ
ቆም ፡ ብዬ ፡ አሰብኩት ፡ የፈጠረውን
ሁሉንም ፡ አዋቁ ፡ ብልህ ፡ መሆኑን
አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ
እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ
ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x)
የሊቅ ፡ ዕውቀት ፡ ቀርቶ ፡ የረቀቀውን
መቼ ፡ ቀላል ፡ ሆነ ፡ የሰውስ ፡ ጥበብ?
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ለዚህ ፡ ድንቅ ፡ ጌታ
ሃሌሉያ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ ሊባል ፡ ነው ፡ ታዲያ?
አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ
እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ
ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x)
|