በለቅሶ ፡ የዘራሁት (Beleqso Yezerahut) - ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ
(Edom Leulseged)

Edom Leulseged 1.jpg


(1)

አንተ ፡ ገናና
(Ante Genana)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤዶም ፡ ልዑልሰገድ ፡ አልበሞች
(Albums by Edom Leulseged)

በለቅሶ ፡ የዘራሁትን ፡ በደስታ ፡ አጨድኩት
ምርኮዬም ፡ ተመልሷል ፡ በብዙ ፡ በረከት
ሚስጢሩ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ የማምለጫው ፡ መንገድ

እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ማለት
ጌታን ፡ ላመስግን ፡ ባልሆነው ፡ በሆነው
በዚያ ፡ ሠፈር ፡ ብቻ ፡ ድልን ፡ ተቀዳጀሁ

ዛሬ ፡ እንደ ፡ ትላንት ፡ መች ፡ አለቅሳለሁ
ቁልፉን ፡ አስይዘኸኝ ፡ የምሥጋናን ፡ በትር
ጠላቴን ፡ ረግጬ ፡ አንበረክከዋለሁ
በፎከረብኝ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ እፎክራለሁ

ከሚውጠው ፡ ጉድጓድ ፡ ከሚያሰጥም ፡ ማጥ
አውጥቶ ፡ አቆመኝ ፡ እግሮቼን ፡ በዓለት
መች ፡ ተንሸራተትኩኝ ፡ በቃሉ ፡ ላይ ፡ ቆሜ
ድልን ፡ ተቀዳጀሁ ፡ እንዲያውም ፡ በአምላኬ

ልግለጥ ፡ ልግለጥ ፡ ምርጡን ፡ የጦር ፡ መሳሪያዬን
ላንበልብለው ፡ ዛሬ ፡ ጠላቴም ፡ ይሸበር
የመንፈስን ፡ ሠይፍ ፡ አጥብቄ ፡ ይዣለሁ
ጠላቴን ፡ ቆርጬ ፡ አጋድመዋለሁ

ከደም ፡ ከሥጋ ፡ ጋር ፡ ውጊያን ፡ አቁሜያለሁ
ነገሩ ፡ ገብቶኛል ፡ አሁን ፡ ነቅቻለሁ
ዘመን ፡ መጣ ፡ መጣ ፡ የዜማ ፡ ወራት
ከሁሉም ፡ ይሰብሰብ ፡ ይግባ ፡ ለአምላክ
ከንፈሮቼን ፡ ልክፈት ፡ አንደበቴም ፡ ያውራው

ቅኔም ፡ ይደርደር ፡ ከዝማሬ ፡ ጋራ
ታማኝነትህን ፡ ማዳንህን ፡ ልንገር
ሌላ ፡ ሰው ፡ አልሻም ፡ እኔው ፡ ነኝ ፡ ምስክር
ቀረ ፡ መሸማቀቅ ፡ አቀርቅሮ ፡ መሄድ
ቀንበር ፡ ተሰበረ ፡ ቀንቅ ፡ ብዬ ፡ እንድሄድ