በአምላኬ (Bamlakie) - ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ
(Edom Leulseged)

Edom Leulseged 1.jpg


(1)

አንተ ፡ ገናና
(Ante Genana)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤዶም ፡ ልዑልሰገድ ፡ አልበሞች
(Albums by Edom Leulseged)

በአምላኬ ፡ ደስ ፡ አለኝ
በፍቅሩ ፡ ረካሁኝ (፪x)

ሕዝብህን ፡ ለማዳን ፡ ፈጥነህ ፡ ትነሣለህ
የተቀባውንም ፡ ትታደገዋለህ
እኔስ ፡ መጠጋቴ ፡ አንተኑ ፡ ላምን ፡ ነው
መፎከሪያዬ ፡ ነህ ፡ የሚነካኝ ፡ ማነው (፫x)

አዝ፦ ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው
ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x)

አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚሆን
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚደርስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚወድ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚራራ (፪x)

አንተ ፡ የሠራኸው ፡ ለእኔ ፡ ተቆጠረ
ይኸ ፡ ደግሞ ፡ ሳያንስ ፡ ስሜ ፡ ተቀየረ
ልሳቅ ፡ እንጂ ፡ በደንብ ፡ በከሳሼ ፡ ላይ
መርገም ፡ ተሰበረ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ
መርገም ፡ ተሰበረ ፡ መድኃኒቱን ፡ ሳይ
መርገም ፡ ተሰበረ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ

አዝ፦ ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው
ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x)

አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚሆን
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚደርስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚወድ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚራራ (፪x)

የጠላቴን ፡ ራስ ፡ አስረግጠኸኛል
ድልን ፡ እያበዛህ ፡ አስደንቀኸኛል
ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ የእኔ ፡ እንደሆንክ ፡ ሳስብ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ አምላኬ ፡ መሆንህን (፫x)

ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው
ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x)

በአምላኬ ፡ ደስ ፡ አለኝ
በፍቅሩ ፡ ረካሁኝ (፪x)