From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ
አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ችሎታህ ፡ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ፡ ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ፡ ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ፡ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)
ከፊቴ ፡ ስትቀድምልኝ ፡ እጄን ፡ ይዘህ ፡ ስታወጣኝ
ያለፈውን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ አሳልፈህ ፡ ስታስቀኝ
ታዲያ ፡ እንደዚህ ፡ አድርገህላኝ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ተነስቼ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አቀርባለሁ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንደዚህ ፡ አድርገህልኝ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ ፀሎቴን ፡ ሰምተህልኝ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ ጠላቴን ፡ አባረህልኝ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞልተህልኝ
አዝ፦ አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ
አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ችሎታህ ፡ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ፡ ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ፡ ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ፡ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)
ሰምተህ ፡ ዝም ፡ ማለት ፡ አታውቅም
ፀሎቴን ፡ አትንቅም
መቼ ፡ ሆኖልህ ፡ የእኔ ፡ ነገር
አቤት ፡ ጉድ ፡ ነው ፡ የአንተስ ፡ ፍቅር
ታዲያ ፡ እንደዚህ ፡ አድርገህልኝ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ተነስቼ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አቀርባለሁ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
አዝ፦ አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ
አንተ ፡ ገናና ፡ ሆይ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ችሎታህ ፡ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ፡ ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ፡ ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ፡ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)
|