አማራጭ ፡ የለም (Amarach Yelem) - ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤዶም ፡ ልዑልሰገድ
(Edom Leulseged)

Edom Leulseged 1.jpg


(1)

አንተ ፡ ገናና
(Ante Genana)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤዶም ፡ ልዑልሰገድ ፡ አልበሞች
(Albums by Edom Leulseged)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው
በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x)

ጌታን ፡ የማያውቅ ፡ በጨለማ ፡ ይኖራል
በምድርም ፡ ሲኖር ፡ ተደናብሮ ፡ ያልፋል
የዓለም ፡ ዝብርቅርቅ ፡ ጊዜያዊ ፡ እኮ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ያለው ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው
በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x)

የፈጠረህማ ፡ እጅጉን ፡ ቢወድህ
አንድያ ፡ ልጁን ፡ በነጻ ፡ እንዲሁ ፡ ሰጠህ
አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጠህ
ምክንያትን ፡ አታብዛ ፡ ሰበብህን ፡ አቁም
ይልቅ ፡ ልቦናህን ፡ ወደ ፡ አምላክም ፡ መልስ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው
በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x)

ነገ ፡ ዛሬ ፡ አትበል ፡ ነገ ፡ የአንተ ፡ አይደለም
የመዳኛ ፡ ሰዓት ፡ ቢኖር ፡ አሁኑኑ ፡ ነው
ሰዓቱ ፡ አሁን ፡ ነው
አምልጠኸው ፡ ውጣ ፡ ያሰረህ ፡ ጠላት ፡ ነው
ትብታብህ ፡ ይፈታል ፡ ኢየሱስን ፡ ጌታህ ፡ ስታደርገው

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው
በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x)