ግራ ፡ ቀኝ ፡ አልልም (Gera Qegn Alelem) - ኤደን ፡ እምሩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤደን ፡ እምሩ
(Eden Emiru)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የኤደን ፡ እምሩ ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Eden Emiru)

አዝ፦ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም
ወደ ፡ ኋላ ፡ ወደ ፡ ፊት
በአንተ ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል
ሰላም ፡ በአንተ ፡ አግኝቷል
በጥያቄዬ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባ
ነገሬን ፡ አሳምሮ ፡ ዓይኔ ፡ በደስታ ፡ አነባ

ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ
አምናን ፡ አሳልፈህ ፡ በዚህ ፡ ያደረስከኝ
ለነገም ፡ አልፈራም ፡ አንተ ፡ እያለህልኝ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ ሳልል ፡ ፀንቼ ፡ ቆምኩኝ

ሰላም ፡ ሆንከኝ (፫x)
ጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ሆንከኝ
እረፍት ፡ ሆንከኝ (፫x)
አባቴ ፡ እረፍት ፡ ሆንከኝ

ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ አንስቼ ፡ አንተን ፡ ልመልከት
ብትዘገይም ፡ እንኳን ፡ መምጣትህ ፡ አይቀር
በመንገድህ/በመቅደስህ ፡ ቆሜ ፡ ጠብቃለሁ
በእርግጥም ፡ ስትመጣ ፡ በዓይኔ ፡ አያለሁ (፪x)

ለምኜ ፡ አንድም ፡ ቀን ፡ አላፈርኩም
ጥያቄም ፡ ሞልቶ ፡ እርፍ ፡ አልኩ
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ዛሬ ፡ ተደላድሏል
አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል (፪x)

አዝ፦ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም
ወደ ፡ ኋላ ፡ ወደ ፡ ፊት
በአንተ ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል
ሰላም ፡ በአንተ ፡ አግኝቷል
በጥያቄዬ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባ
ነገሬን ፡ አሳምሮ ፡ ዓይኔ ፡ በደስታ ፡ አነባ

ሰላም ፡ ሆንከኝ (፫x)
ጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ሆንከኝ
እረፍት ፡ ሆንከኝ (፫x)
አባቴ ፡ እረፍት ፡ ሆንከኝ

ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ
አምናን ፡ አሳልፈህ ፡ በዚህ ፡ ያደረስከኝ
ለነገም ፡ አልፈራም ፡ አንተ ፡ እያለህልኝ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ ሳልል ፡ ፀንቼ ፡ ቆምኩኝ

ምድረ ፡ በዳዬን ፡ ታለመልማለህ
ባዶ ፡ ሸለቆዬን ፡ በውኃ ፡ ትሞላለህ
በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፪x)

ወዳጅ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማን ፡ አለ
ሚስጥር ፡ ተካፋይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ሁሉን ፡ ነገር ፡ አውቀህ ፡ ትመዝናለህ
በእውነትም ፡ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ

ወዳጅ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማን ፡ አለ
ሚስጥር ፡ ተካፋይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ሁሉን ፡ ነገር ፡ አውቀህ ፡ ትመዝናለህ
በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ

ለምኜ ፡ አንድም ፡ ቀን ፡ አላፈርኩም
ጥያቄም ፡ ሞልቶ ፡ እርፍ ፡ አልኩ
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ዛሬ ፡ ተደላድሏል
አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል

ምድረ ፡ በዳዬን ፡ ታለመልማለህ
ባዶ ፡ ሸለቆዬን ፡ በውኃ ፡ ትሞላለህ
በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ