ቃል ፡ ያልቃል (Kal Yalkal) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(2)

2
(2)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

በወጀቡ መሃል በአስጨናቂው ሞገድ
ና ብሎ ጠርቶኛል ወደ እርሱ እንድራመድ
በማዕበሉ ውስጥ በእጆቹ ደገፈኝ
የአምላኬ እርዳታ ሁሉን አሳለፈኝ

አዝ:- ቃል ያልቃል ሊገልፀው ማዳን የእሱን ስራ
ከሁኔታ በላይ መለኮት ሲሰራ
በሚታየው ዓለም ማይታሰበውን
አቤት ስንቱን አየሁ ድንቁን አሰራሩን (2X)

የሌለውን ነገር ካለመኖር ጠራ
በንግግር ብቻ ሰማይ ምድርን ሰራ
በሰው ዘንድ ካለቀ በቃል ከተቋጨ
ከደረቅ አለት ላይ ምንጭን አመነጨ

አዝ:- ቃል ያልቃል ሊገልፀው ማዳን የእሱን ስራ
ከሁኔታ በላይ መለኮት ሲሰራ
በሚታየው ዓለም ማይታሰበውን
አቤት ስንቱን አየሁ ድንቁን አሰራሩን (2X)

የሚሳነው የሌለ ከልካይ የለ ለሃሳቡ
ደካማን የሚደግፍ የሚቆም አጠገቡ
አሰራሩ አይመዘን በስሌት አይለካ
ለሚጠሩት ስሙን አለኝታ የሚያስመካ

አዝ:- ቃል ያልቃል ሊገልፀው ማዳን የእሱን ስራ
ከሁኔታ በላይ መለኮት ሲሰራ
በሚታየው ዓለም ማይታሰበውን
አቤት ስንቱን አየሁ ድንቁን አሰራሩን (2X)