ኃይል ፡ የእግዚአብሔር (Hayl Yegziabher) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(2)

2
(2)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ይህን ብቻ
እርሱ እንደሆነ የሁሉ ነገር መርቻ
ሃይል የእግዚአብሔር ነው በምድር በሰማይ
ሁሉን ማድረግ የሚችል የለ ከእርሱ በላይ
    
       1.በሰራዊት ብዛት አይድንም ንጉሱ
    ጦረኛው ከሸሸ አይረዳው ፈረሱ
    ዘየድኩኝ ለራሴ እኔ ግን እንደቃሉ
    ልቤን በእርሱ ጥዬ በእግዚአብሔር በሃያሉ

ሃይል ሁሉ የእርሱ ነው ብርታት ሆነ ጉልበት
የሰማይ ምሰሶዎቹ የፍጥረታት መሠረት

አዝ:- በክንዱ ተደግፌአለሁ ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ ሃይል የእግዚአብሔር ነው (2X)

እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ይህን ብቻ
እርሱ እንደሆነ የሁሉ ነገር መርቻ
ሃይል የእግዚአብሔር ነው በምድር በሰማይ
ሁሉን ማድረግ የሚችል የለ ከእርሱ በላይ


    2. ሃያላንን ፈጥሮ ሃይሉን የገለጠ
አስቦ በቃሉ ፍጥረት የቀረፀ
የሰማይ ስርዓት የምድር ሃይል ጥግ
ሁሉ ………

ሃይል ሁሉ የእርሱ ነው ብርታት ሆነ ጉልበት
የሰማይ ምሰሶዎቹ የፍጥረታት መሠረት

አዝ:- በክንዱ ተደግፌአለሁ ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ ሃይል የእግዚአብሔር ነው (2X)

ይህንን እውነት ተረድቼ አይቼ
አልሸበርም ሌላውን ሰግቼ
የያዝኩት ብርቱ ሃያሉ ጌታዬ
እግዚአብሔር ነው ሃይሌ መመኪያዬ (2X)

አዝ:- በክንዱ ተደግፌአለሁ ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ ሃይል የእግዚአብሔር ነው (2X)