አመልክሃለው (Amelkihalew) - ኤባ ፡ ድንኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤባ ፡ ድንኤል
(Ebba daniel)

Lyrics.jpg


(2)

2
(2)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤባ ፡ ድንኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Ebba daniel)

ትላንትን እንዳመለኩህ ዛሬም ላምልክህ
የአንደበቴ ፍሬ ይባርክህ ክብር ይሁንልህ
በሰጠኸኝ እድሜ አመስግኜ
መቼ ረካሁ ከልቤ አምልኬ
በሰጠኸኝ ዘመን አመስግኜ
መቼ ረካሁ ከልቤ አምልኬ

ጎጆውን ሊያፀና ሰው ያቆማል ምሰሶ
     ምስጋናህም ውስጤን አነፀኝ አቆመኝ መልሶ
     የአምልኮ ቤቴ በደስታ በሃሴት ታጅቦ
      መስዋዕት ያቀርባል ዜማን ቅኔን አንግቦ

አዝ:- እግዚአብሔር ሆይ አመልክሃለው አመልክሃለው
አንተ አምላኬ ነህ አከብርሃለሁ
አከብርሃለሁ
ምክንያት ሁኔታ ሳይሆነኝ ልኬ
አመልክሃለው ጌታ አምላኬ (2X)

ትላንትን እንዳመለኩህ ዛሬም ላምልክህ
የአንደበቴ ፍሬ ይባርክህ ክብር ይሁንልህ
በሰጠኸኝ እድሜ አመስግኜ
መቼ ረካሁ ከልቤ አምልኬ
በሰጠኸኝ ዘመን አመስግኜ
መቼ ረካሁ ከልቤ አምልኬ

ሁሉ የተሰጠኝ የተደረገልኝ
    የገባኝ ሰው ሆኜ ለማምለክ ኧረ እንዴት ሊከብደኝ
     ከሁኔታ በላይ መዘመር መቀኘት ተምሬ
     ዛሬም ላወድስህ እጥፉን ደርቤ ጨምሬ

አዝ:- እግዚአብሔር ሆይ አመልክሃለው አመልክሃለው
አንተ አምላኬ ነህ አከብርሃለሁ
አከብርሃለሁ